Post

ሊገድሉ ያሰቡትን ኣማራ … “ነፍጠኛ” ነው ይሉታል

ሊገድሉ ያሰቡትን ኣማራ … “ነፍጠኛ” ነው ይሉታል

By Admin

ተረቱ እንኳን፦ ሊበሉ ያሰቧትን ኣሞራ … ነበር። ዘንድሮ ግን፦ ሊበሉ ያሰቡትን ኣማራ “ነፍጠኛ” ነው እያሉ እንደ እንስሳ በካራ ይበልቱት ጀምረዋል።

ግን ጎበዝ … ቤንሻንጉል ከኢትዮጵያ ድንበር ምን ያህል ይርቃል? ከመሬት ጋር አብሮ ዞሮ መተከል የግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ሆነ እንዴ? እንዴት ነው የኢትዮዽያ መንግስት እዚህ ክልል ውስጥ ገብቶ ህግ ማስከበር የተሳነው? ትላንትናስ እሺ … ሰበብምክንያታቸው ሸረሪት ያሉዋት ህወሃት ነበረች። ዛሬስ ይኽን የሰው ስጋ እንደ ተክል ቅጠል የሚቅመውን ጥቁር ጢንዚዛ ማን ብለው፣ ምን ምክንያት ሊሰጡን ነው? በግሬደር እየተዛቀ የሚቀበረውኮ ቢያንስ ለኣንድ ቤተሰብ አባት፣ እናት፣ ወንድም፣ እህት ወይንም ልጅ የነበረ የውድ ሰው አስክሬን እንጂ፥ የቻይና bamboo ዛፍ ፍሬ አይደለም … ከኣምስት ዓመት ቦኃላ ተመልሶ የሚበቅል የሚመጣ።

መቼም፦ ህዝብ በስለት ተበለተ፣ በቀስት ተቀሰተ ተብሎ ለአጥንት አልባው ተሳቢ ኣዴፓ “አቤት!” አይባልም። ውክልናቸው ለሰብል እንጂ ለሰው እንዳልሆነ እስኪመስል ቀን ቆመው፣ ማታም ተኝተው የሚያሳስባቸው፥ የገዳም ከበሮ የሚያክለው ከርሳቸውን የሚሞሉበት እህል ነው። ዛሬም ቤዛህን ከመንግስት በተለይም ደግሞ ከኣዴፓ የምትጠብቅ ኣማራ ካለህ ግን በቁምህ ነፍስይማር!” ልበልህ። ምክንያቱም፦ እስከ አሁንም በህይወት የመቆየትህ ሚስጢር የአምላክ አስተዋይነት ነውና። ልቡን አይቶ እባብን እግር እንደከለከልው፥ የኣንዳንዱንም ጭንቅላት ደንዳናነት ተመልክቶ ቀንድ ነሳው እንጂ እንደ አጐነባበሱ … የመተከል አይደለም የመተማም ኣማራ ተረት ሆኖ ይቀር ነበር። እዚህ ላይ መርዛማዎቹን አቶ ሽመልስ አብዲሳንና አቶ ታዬ ደንደአን ላስታውስህ ግድ ይለኛል።

እኔ ግን … ዛሬም ቢሆን በፅኑ የማምንበት ሐቅ ይህ ነው፦ በሰሜንም ሆነ በደቡብ፣ በምስራቅም ይሁን በምዕራብ፣ በየትኛውም አቅጣጫ በኣማራው ላይ እየተሰነዘረ ያለውን ጥቃት ለማስቆም በሁልቱም አፍ የተሳለ ስይፍ የታጠቀ ፀበኛ እንጂ በሁለት አፍ የሚያወራ ፀሎተኛ መንግስት አይቻለውም። ከትንሹ ጋር ትንሽ፣ ከትልቁ ጋር ትልቅ ሆኖ መዋል አስተዋይነት ከሆነ፤ ለፀበኛውም ፀበኛ ሆኖ መገኘት ኩነኔ አይሆንም

ከኣስርቱ ትዕዛዛት ኣንዱ አትግደል እንጂ አትጋደል አይልም። ተጋድሎህ አግባብ ሲሆን ደግሞ፥ በገባዖን ላይ እንዳደረገው፥ አምላክም የፈጠረውን ዓለም የሚያስተዳድርበትን ህግ ሽሮ …  በምሽትም ፀሐይን እንዳትጠልቅ ያደርጋታል። እኔን ባታምን፣ እስራኤላዊውንም ሙሴን ለማግኘትም ብትቸገር፥ አሻጋሪህን ጠቅላይ ሚንስትር ጠይቃቸው፤ ምዕራፍ ጠቅሰው፣ ቁጥር ቆጥረው በሚገባ ያስረዱሀል። አስተውል! ሀይማኖት፦ ነፍስና ስጋን ከሀጢያት ሰንሰለት አርነት ማውጫ እንጂ የባርነትን ሞፈር መሳቢያ ቀንበር አይደለም። ደግሞም፦ እኔም አንተም ስንተዋወቀው፥ ስሙን የሰላም አለቃ ብቻ ሳይሆን ብርቱ ተዋጊ ብሎም ነው የነገረን። ታዲያ ምንድነው ክንድህን ያሰረው? የዱሮው የአያት፣ ቅደመአያቶቻችን ዘመን አልፏል። የዘር አጋንንት እንደ virus እና bacteria መድሐኒቱን ተላምዶ እራሱን ቀይሯል። ይኽን ክፉ መንፈስ በጥይት እንጂ በፀሎትም ሆነ በምክር የሞከረ ከማስለቀቁ በፊት እራሱ ቀድሞ ያልቃል። መዳንህ በመዳፍህ ነው … ወገኔ።

የቅሬታ ጽሑፌን ከማጠቃለሌ በፊት ግን፥ እስቲ እናንተ አጥንትአልባ ኣዴፓዎችን ኣንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ። መቼም፦ እንደ ዘበት የሚያልፈው የምስኪኑ ገበሬ ነፍስ፣ በከንቱ የሚፈሰው የደሃአደጉ ደም የሚቆጫችሁ መቼ ነው? ብዬ የምጠይቅ ቅልአእምሮ ያለኝ ቂል አይደለሁም። ግን ባይሆን፦ ልክ እንደ አቶ ሽመልስ አብዲሳ … አቶ አሻድሊ ሀሰንንም ባህር ዳር ድረስ ጠርታችሁ ካባ የምታለብሷቸው መቼ ነው?

Comments are closed.