
By Admin
ተቀበል …
አፋፉ ላይ ቆሜ … ሳየው አሻግሬ
ሰብሮ ሲከምረው … የመሰለኝ አውሬ
ስጠጋው ለየሁት … አወይ መታወሬ
ለካስ ሰውየው ኖሯል … የሚሉት “አጅሬ”
ተቀበል …
ድንገት ሳይታሰብ … ብልጭ! ያለ ‘ለታ
ከጉም ደመናው ኣፍ … ተመዞ ሲወጣ
እንደ ደረቅ እንጨት … ሰንጥቆ ‘ሚጥለው
ፋኖ መብረቅ እንጂ … ማን ነው ‘ሰው’ የሚለው?
ያን የእሳት ፍላፃ … ስጋ የሚያለብሰው?
ተቀበል …
ንቆ ቁጭ ቢል … ፍርሃት መስሏቸው
ሲወዛወዙ … ምድር ጠቧቸው
ደግሞ ተነሳ … ሊያስቀምጣቸው
ከደጅ ጉድጓዱ … ሊወዝፋቸው
ተቀበል …
ያልበላውን ሲያክ … በጥፍር ጥርሱ
ለያዥ ቸግሮ … ለገናዥ ቄሱ
መጣ ያ ፋኖ … ፎጣ ለባሹ
በልኩ ቀዶ … ከፈን አልባሹ
ተቀበል …
ለውብ ሳዱላ … ትላንት ተድሮ
ማልዶ ሸፈተ … ክላሻ አፍቅሮ፥
ድሮስ መች ለምዶ … መኝታ ከአልጋ
ተዉት ከሜዳው … ሲያጋድመው ይንጋ
ተቀበል …
ጀግና እና ጀበና … መለየት አቅቶት
አለቀ የኣብይ ዘብ … ጎጃም ገብቶ አዳልጦት ፥
እንዳላ’ሳደረ … ከጎን ሆኖ ጥላ
ጎንደሬ ጉድጓድ ነው … ይውጣል ሲጣላ
ተቀበል …
መሬ ለጠላቱ … ወዳጅ ለወገኑ
መገን የኣማራ ልጅ … ዱር- ጫካ ድንኳኑ
*** (የቀለም ቃላቱን ስውር ፍቺ ለኣንባቢ ትቼዋለሁ)