
By Adimin
ሰሞኑን አጥጋቢ ምክንያት ካልነበረው የተራዘመ የኢንተርኔት መቆራረጥ ተነስቼ ስለ ሀገራችን ሁኔታ ጥቂት መላምቶች ነበሩኝ። ከዚህም አልፎ፦ በጠቅላይ ሚንስትሩ አባት (ነፍስ ይማር) የቀበር ስርዓት ላይ፦ ጠቅላይ ሚንስትሩና አቶ ለማ መገርሳ በተለያየ ሰዓት መገኘት ለመደበኛ ደህንነት ታስቦ የተደረገ ጥንቃቄ ነው ብዬ ባምንም “ይኽን ያህል ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን የሚችል የሚጠበቅ ግዙፍ ጥቃት ይኖር ይሆን? ” ስል መጠየቄ ግን አልቀረም።
ያም ሆኖ፦ ከትላንት በስቲያ በኣማራ ክልል የተከሰተውንና መንግስት “መፈንቅለ-መንግስት” ያለውን ክስተት ስሰማ ግን የፌደራል መንግስቱ ድራማ እንደሆነ ቅንጣት ጥርጣሬ አልነበረኝም፤ አሁንም የለኝም። ሌላ መገለጫ ቃላት ጠፍቶ የግድ መፈንቅለ- መንግስት የሚል ስያሜ እንስጠው ካልንም፥ መፈንቅለ መንግስት አድራጊው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ (ነፍስ ይማር) ሳይሆኑ፥ ድርጊቱን ከማንም በፊት ተሽቀዳድመው ያወገዙት፣ ያለ ስሙም ስም የሰጡት ፌደራል መንግስቱና የአዲስ- አበባ ክልል መስተዳድር ናቸው።
እውነት ለመናገር፦ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ “Team Lemma ” የሚለውን ስብስብ የሁለት ግለሰቦች ድምር ብቻ አድርጌ እስክመለከት ድረስ በጠቅላይ ሚንስትሩና በአቶ ለማ መገርሳ ላይ ትልቅ እምነት ነበረኝ። ታዲያ ምን ያደርጋል … “ጥቂት የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቶ ያገሙታል ” እንደሚል፦ ዛሬ የጄነራል አሳምነው ፅጌን መገደል ስሰማ – ያንን የሽቶ ብልቃጥ ሰብሬ፣ እምነቴንም ከውሃው ጋር አብሬ አፍስሼዋለሁ።
ጄነራል አሳምነው ጽጌን ከኃላፊነታቸው ማንሳትም ሆነ ማስነሳት የኣማራ ህዝብ ፍላጐትና መብት ብቻ ሆኖ መከበር ሲኖርበት፥ “በክልሎች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አልገባም ” የሚለን የፌደራል መንግስት ግለሰቡን ለማንሳት ወይንም በግልፅ ቋንቋ በወቅቱ በነበሩት የአዴፓ አመራር አስፈፃሚነት ለማስነሳት ለምን ፈለገ? በዕለቱ የአዴፓ አመራሮች ከተቀመጡበት ጥቂት የስብሰባ አጀንዳዎች መካከል በባህር ዳር ከተማ ለመካሄድ የታቀደለት የአዲስ-አበባ ባልደራስ ስብሰባ ” አካሄድና ፀጥታ” አንዱ እንደሚሆን የግል ጥርጣሬዬ ነው። ይህ ደግሞ ጄነራል አሳምነው ጽጌን በቀጥታ የሚመለከት ጉዳይ እንደሚሆን፣ ጄነራሉም ለዚህ ስብሰባ ሰበብ-አስባብ ፈጥረው ወይ ደግሞ ትዕዛዝ ተቀብለው እንደ አዲስ-አበባ ፖሊስ ባለቀ ሰዓት የስብሰባ አዳራሹን አስከብበው ለመከልከል ፍቃደኛ ይሆናሉ የሚል ግምት ፈፅሞ አይኖረኝም። በዚህና በሌሎች ፍፁም ምክንያታዊ አቋማቸው ላይ ጥቂት ባለስልጣናት በሚይቀርቡት ስሞታ ተገዝቶና ተገዶ ፌደራል መንግስት በኣማራ ክልል ህዝብና ፍላጎት ላይ መፈንቅለ መንግስት ማድረግ (ማስደረግ) ስልጣን አለውን?
ፌደራል መንግስቱ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ግፍና መከራ የሚፈለግ ወንጀለኛ ግለሰብን ትግራይ ክልል ገብቶ ለማሰር በብርክ ተመቶ፥ እንዴት ኣማራ ክልል ውስጥ ለህዝብ የመኖርና ያለመኖር ዋስትና የሚደክምን ባለስልጣን በጠራራ ፀሐይ ገድሎ ይወጣል? መልሱ ግልፅ ነው! አዴፓ ፈርስ እንጂ ነፍስ የሌለው የኦዴፓ ገዳዮች ፈረስ ነው።
ሌላው የታዘብኩት፥ ነገር ግን የሚጠበቅ ስለሆነ ያልገረመኝ ጉዳይ ቢኖር፦ እኚህ ጠቅላይ ሚንስትር ወደ ስልጣን ከመጡበት ዕለት ጀምሮ በየትኛውም የስራ አፈፃፀም መመሪያም ሆነ ተግባር ፍፁም ተቃራኒ አቋምና አመለካከት የሚይዙት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ ብሔር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ድርጊትና ገለፃ ጋር ተስማምተው መግለጫ የሰጡበት ጉዳይ ቢኖር ይህ የ “መፈንቅለ-መንግስት” ልቦለድ ትርክት ብቻ ነው።
እንደው ለመሆኑ፦ ዛሬ ጄነራል አሳምነው ፅጌን በማስገደል የኣማራን ህዝብ አጥርና ቅጥር ያፈረሰው ፌደራል መንግስት፥ ነገ ምስኪኑን ገበሬ በብሔርተኞች ጥይት ሲያስፈጀው፦ “በባህር-ዳርና በአማራ ክልል መንግስት ፈቃድ ከሰጠው አካል ውጪ ማንም የጦር መሳሪያ ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ” ብለው ድርጅታዊ መግለጫ በመስጠት የጄነራሉን አፈና አመቻችተው ወደ አሜሪካ እብስ ያሉት፣ በደመቀበት አብረው የሚያዳምቁት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩም ሆኑ ነገሩ ወደ አልታቀደ መስመር ተጠማዞ ህይወት ሲጠፋ ከብርሃን ፈጥነው ለጌቶቻቸው የምላስ ሽፋን የሰጡት አቶ ንጉሱ ጥላሁን ውዴት ይሮጡ ይሆን? ወደ ባሌ ወይስ ወደ መቀሌ?
ኣማራ ከሆንክ ስማኝ! ኢትዮጵያዊ ሆነህ እንደ ኢትዮጵያዊ በክብር መኖር ከተነፈክ፥ ኣማራ ሆኖ እንደ ኣማራ መጋደል ብቸኛ ምርጫህ ነው! የጄነራል አሳምነው ፅጌን ደም ግንባራቸውን ተቀብተው እንደ ህንድ ሙሽራ እንዲደምቁበት ለብሔርተኞቹ አገልጋይ ለአዴፓ ትተህ ነፍጥህን አንሳ! በባርነት ሰገነት ኖሮና ሸምግሎ ከሞተ አዛውንት ይልቅ፥ በነፃነት ጎጆ ተውልዶ በጨቅላነቱ የተቀጨ ህፃን ዕድሜውን ጠግቦአል ዓለሙንም አይቷል!
ከዚህ ሁሉ ክህደት ቦኋላ በፌደራል መንግስቱም ይሁን በአዴፓ ላይ እምነት ያለው ኣማራ እሱ እንደ ጣና ኣረም ነው – እምቦጭ! መነቀል መወገድ ያለበት!
ተፈንቃዩ ፈንቃይ
ፈንቃዩም ተፈንቃይ
ሆኖ ሲተረክ ባይ
ኢትዮጵያን አስቤ
መጣ በምናቤ
ያ ምስኪን እንስሳው
ከንቱ የሚደክመው
ጭራውን ተናክሶ የሚሽከረከረው