Post

የሰው ልጣጭ!

የሰው ልጣጭ!

By Admin

ተግባርና ምግባር እንጂ ዕድሜና ስልጣን አያስከብርም። በእኛ መካከል፦ በምድር ላይ ቀድሞ የተራመደም ሆነ የሚራመድ፥ በሉሲፈር ዘመን እና ስልጣን ልክ የተፈጥረ ማን ሰው አለ? ይህን ብርሃንተሸካሚ የነበረ መላዕክት ሲመጣ እጅ ነስተን፣ ሲሔድ ከመቀመጫችን ተነስተን ልናስተናግደው ይገባልን?

ሐቁን ግብረገባዊ ለመሆን የቱንም ያህል ገፍተን ልናርቀው ብንሞክር እንኳ፥ እንደ አማራተፈጥሮ እንደ አሳማእየኖረ ያለውን አዴፓ ለመግለፅ የተገራ ቃል ከመፈለግ አልማዝ ቆፍሮ ማውጣት ይቀላል። ስለዚህም ክብር ለሚገባው ብቻ ክብርን እንሰጣለንብለን እሪያዎቹን በተግባርና ምግባራቸው ልክ መግለፅ ዋልጌነት አይሆንም።

በመጀመሪያ ግን ስለ ፅሑፌ ርዕስ ምንጭ ትንሽ ፍንጭ ልስጥ። ከግለሰቡ ጋር ያለን ትውውቅ በድህረገፅ የተጀምረ ቢሆንም፥ የዓላማ አንድነት ግን ኣንድ ደረጃ አሻግሮት አልፎ አልፎም ቢሆን በቀጭኑ ሽቦ ሃሎእንባባላለን። ቤተሰቡ፥ በተለይም እናቱ እንዲያነብላቸው ከሚመርጧቸው መጣጥፎች መካከል እኔም ድርሻ እንዳለኝ ነግሮ አስተዋውቆኛልና በመስቀል አወደዓመት ማምሻ እንኳን አደረሶዎት!” ለማለት ደውዬ ጥቂት አወጋን። እኚህ እናት ስለፖለቲካ ያላቸው ጥልቅ ግንዛቤ እንደ ኑሮዘዴ ፆታዊና ተፈጥሮአዊ ይመስላል። ለነገሩ … ኑሮዘዴም በሉት የአካል እንቅስቃሴ ደግሞም ውዝዋዜ፥ ከረጅሙና ከሰፊው የፖለቲካ እጅ ሮቆ ያለው የሰማዩ ዙፋን ብቻ ነው። ይህ ያልተዋጠለት አንባቢ፥ በየአመቱ በየአህጉሩ የሚደረጉትን የስፖርትም ሆነ የሙዚቃ ውድድሮችና የአሽናፊዎች ምርጫ (ለምሳሌ Eurovision Song Contest) መመልከቱ ግንዛቤውን ያሰፋለታል።

እናም … ከእኚህ እናት ጋር ጥቂት እንዳወራን … ምን እስኪሆን ነው የምትጠብቁት ልጄ? ኑ እንጂ … ይኸው እሱም ታናሹም አለ … ውጡ! ቢገድሏችሁም ለሀገራችሁ፣ ለሀይማኖታችሁ ነው!አሉኝ መረር ብለው። እኔም ፍርሃት እንዳይመስላቸው ብዬ ልክ ብለዋል እናት፤ ግን አደባባይ ወጥቶ የሚናገር ጀግና አሁንስ መች ጠፋ? ቢደነዝዙና ቢደንዙ ነው እንጂ በጠቅላይ ሚንስትሩም ሆነ በየቢሮው የተቀመጡትስ ባለስልጣናት የዚሁ የሚሳደደው፣ የሚገደለውና የሚቃጠለው ዘርና ሀይማኖት ክፍይ አይደሉብዬ መልስኩ። ከዚያኛው የስልክ ጫፍ በብስጭት … ኤጭ! የሰው ልጣጭ!የሚል መልስ ተቀበልኩ። ወዲያውም … ይቅርታ አድግልኝ ልጄ … ስራቸው ሁሉ አልጥምሽ ቢለኝ ንድድ ብሎኝ ነውአሉኝ። እውነት ለመናገር የእኚህን እናት ጆሮ አክብሬ እንጂ በተራዬ እኔም … ሽንታም!” ብዬ ብጨምርበት ከተራ ስድብ አይቆጠርብኝም ነበር። አዎና … ለሀጫም፣ ሽንታምሌላም ሌላም አዴፓ ከራሱ አልፎ ለሰፊው የአማራ ህዝብ ያወረሰው የወል መጠሪያ ነው። ዛሬ ላይ ደግሞ ከኦህዴድ የሚጣልላቸውን የተጋጠ አጥንት ሲቆረጥሙ አፋቸው አፍታ አግኝቶ ተከፍቶ አለን!” እንኳን ማለት ስላልቻሉ … እዚህም እዚያም ኣማራ የለም!” የሚል single እያዳመጥን ነው። ህወሃት በዘረኝነት፣ አዴፓም በዘረቢስነት እኩል የሚከሰሱ እኩይ ድርጅቶች ናቸው።

ያለፉትን ሃያሰባት አመታት በጋራ የመከራ ምዕራፍ ብንደመድመው እንኳ፤ የመደመር አብዮት ከፈነዳ (ከመጣ) ወዲህ ኣማራው ከስድብ፣ ከመፈናቀል፣ ከእስር፣ አልፎም ከግድያ ሌላ ከዚህ መንግስት ምን በረከት ወረደለት? በክልሉ፦ ከባለስልጣን እስከ ገበሬው እንደ ገበሎ ታድኖ ይወድቃል። እውነት ለመናገር፥ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እግር ኣንድ የሱማሌ ወይንም የትግራይ ክልል ባለስልጣን ቢሆን ኑሮ፥ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጓዳቸው እንኳ ለትዳር አጋራቸውም ደፍረው በጆሮዋ የማይተነፍሱትን ስድብ በብሔሩ ላይ እንደወረደ በአደባባይ አያወርዱበትም ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን አሳማው አዴፓ እንዳልሰማ ዛሬ ድረስ የእሬቻን ግብር ያኝካል። አዴፓ አደባባይ ወጥቶ እንደ ውሻ ቡችላ የሚያላዝነው ወንበሩን ሲነጠቅ ወይንም ደግሞ በዝውውር ሰብበ ጥቅሙ ሲጓደል ብቻ ነው። አንዳንዴ የአቶ ደመቀ መኮንን’ን አንደበትአልባነት፣ የአቶ ንጉሱ ጥላሁን’ን ጥላቢስነት ስመለከት፥ በእውነት እነ አቶ ታደሰ ጥንቅሹ በከንቱ ታሰሩ እላለሁ።

ኣማራውን ወክሎ ለመናገር ድምፅ ባይኖረኝም ደም አለኝና፥ እስቲ እግረመንገዴን ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ ይኸቺን ላቀብላቸው። ነፍጥ አንስቶ መተኮስ፥ mic ጨብጦ ከመፎከር በእጅጉ ይለያል። በኢትዮጵያዊ ባህላችን የሚያሳፍረው ንፍጣምነት እንጂ ነፍጠኛነት አይደለም። እኚህን ግለሰብ ሳስባቸው፥ አንድ የቢሮ ወረቀት ለመፈረም ምክር ፍለጋ ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩና ወደ ክቡር ዶክተር ለማ መገርሣ ኣንድ መቶ የስልክ ጥሪ የሚያደርጉ ይመስለኛል። ከተሳሳትኩ ፀሐፊያቸው ታርመኝ። የጊዜ ሹመት በራስ የመተማመንን ብቃትሚዛን ውስጥ ስለማያስገባ ነው እንጂ፥ አቶ ሽመልስ አብዲሳም ሆኑ አቶ አዲሱ አረጋ አይደለም ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብ – ለራሳቸው ቆዳም እጅግ በጣም ይጠባሉ።

አዲስአበባ ትላንትም፣ ዛሬም፣ ወደፊትም ኢትዩጵያየሚባል ባለቤት አላት፤ ለጋብቻም ሆነ ለጉዲፈቻ እጅግ ረፍዷል። እንደው የZeus ልጅ Ares ጦር አዝምቶብን ይህን ቅዥት እናልመው ብንል እንኳ፦ ሸገር የአቶ ሽመልስ አብዲሳ ሞጋሳበሆነች ጀንበር እናት ሀገር ትፈታለች። እርግጥ ነው … እናት ሀገር በተፈታች ዕለት ደግሞ ኦሮሚያ ትፀነሳለች። እናት ሀገር በተፈታች ዕለት የተፀነሰችው ኦሮሚያ ደግሞ ውልደትን ሳታይ በወራት ዕድሜ ትጨነግፋለች። ያ ደግሞ የምስራችነቱ ለግብፃዊው ኦሮሞ እንጂ ለኢትዮጵያም ሆነ ለኢትዮጵያዊው ኦሮሞ መሽቶ በነጋ ቁጥር በየማለዳው የምናለቅሰው መርዶ ሆኖ ይቀራል።

ከጽሑፌ መነሻ ምክንያት ብዙ ሳልርቅ፥ በአዴፓ በረት ላሉት እሪያዎች ለእርማትም ባይሆን ለግንዛቤ የመጨረሻ መልዕክቴን አስተላልፌ ላብቃ፦ በነፃነት እየተመላለሱ በቀን 40 ጊዜ ቁጭ ብሎ ከመሽናት እንደ ክርስቲያን ታደለ በእስር ሆኖ፣ ጠመንጃ ባቀባበለ የኦህዴድ ወታደር ፊት በቀን አንድ ጊዜ ቆሞ መሽናት የወንድነት ክብር፣ የኣማራነት ደም ነው!

እውነት ለመናገር ይውደም ይለምልምየሚል መፈክር ያልኩብት ጊዜ የለም። ዛሬ ግን … ለወደፊቱ ትውስታዬ የሚሆነኝ ኣንድ እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ። የአደርባዩ አዴፓ የስልጣን ወንበር ይውደም! የጄነራል አሳምነው ፅጌ አፀደመቃብር ይለምልም!

Comments are closed.