Post

የሳምንቱ ስልኬ XI

የሳምንቱ ስልኬ XI

By Admin

   ሄሎ

  ሄሎ፥ እንደምን አለህ?

   እንደፈለኩት ብዬ እንዳልልህ፥ አቶ ታዬ ደንደአ ብቻ ናቸው እንደልባቸውውሎ ማደር የተፈቀደላቸው። ምነው ግን ጠፋህ?

  የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ናችሁ ብዬ ጊዜ ላለመሻማት ነዋ

   ወይ ቅ ስ ቀ ሳ መቼ ተኝተን ነው የምንቀሰቀሰው? ቀን ዕረፍት፣ ማታ እንቅልፍ አጥተን፥ በፅንፈኛ ጫካ ለጫካ ስንባረር አይደል እንዴ ውለን የምናድረው ? ባይሆን ራዲዮና ቴሌቪዥኑን ፈቅደውልን እኛ በቀሰቀስናቸው

  ከነቁልህ ሞክር፤ እኔ ግን የራድዮኑን ሞገድ ትተህ፥ በመደመር መንገድ ብትሞክር ነው የሚያዋጣህ የሚመስለኝ

   ምንድነው የመደመር መንገድ?

  ተማፅኖ

   እየቀለድክ ነው?

  አንተ ነህ እንጂ የምትቀልደው፤ እንደጎርፍ የሚፈሰውን የንፁሐንን ደም በኣይኑ እየተመለከተ፥ በጀርባው ለሽ ብሎ ተኝቶ የሚያንኮራፋን ፖለቲከኛ በራዲዮ ልቀስቅስ የምትል ቀልደኛ። በስልጣን ወንበራቸው እስካልመጣ ድረስ፦ የአንተ አራጅ ሸኔለእነርሱ አራሽ ገበሬነው፤ ማን ይነካዋል? የመደመር መንገድ ማለት ይኼ ነው፤ ከአጣዬ አትማርም? ለስልጣን እስካላሰጋ ድረስ … ክላሽ ያነሳን ነፍሰ ገዳይ ክርስትና አንስቶ መመለስ

   እሱንስ ልክ ብለሀል። አሁን አሁንማ ጠቅላይሚንስትሩ ሲያወሩ ስሰማ፥ ዶ/ር ኢንጂነር ሳሙኤል ዘሚካኤልን እየመሰሉኝ ተቸገርኩ

  ብቻህን አይደለህም። ይልቅ … ምርጫችሁ ደረሰ አይደል?

   የምን ምርጫ ነው የምታወራው? ክፍት የሥራ ቦታ አትለውም?

  ምነው? ዕጩዎች የሚመዘገቡት በትምህርት ማስረጃ ነው ተባለ እንዴ?

   እንደዛ በለው። ተወዳዳሪ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን የሚያስተዋውቁት፦ ማን ምን አይነት ማህበራዊና ግለሰባዊ ስብዕና አለው? ለሚመርጠው ህዝብ ፍላጎት ውክልናስ እስከ ምን ድረስ ሊታመን ይችላል? የሚለውን በማስገምገም ሳይሆን፥ የእኔ እጩ ፕሮፌሰር ነው፣ የእኔ ደግሞ ማስተር፣ የእኔ ደግሞ ሚስቱ ባለ ድሪ እሱም ባለ ዲግሪ ናቸው … እያሉ ሆኗል። የኢትዮዽያና የህዝቦቹዋ ነቀርሳ ተማርኩ የሚለው ምሁር እንደሆነ የማናውቅ ይመስል

  ተው! ተው! ምሁሩንማ አትሳደብ

   ስድብ ነው እንዴ ይሔ? ግን አልፈርድብህም፥ ዘንድሮ እውነትን መናገር ስድብ ሆኗል

  ከምሁሩ ላይ ምላስህን አንሳ እንጂ … እውነት አትናገር መቼ አልኩህ?

   እና? ከትላንትና ታሪክ እስከ ዛሬ እውነታ ሀገሪቷ እንዲህ ያለ ትርምስ ውስጥ ገብታ እንድትዳክር ያደረጋት አርሶአደሩ ነው ልትለኝ ፈለክ?

  እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ይህን ያህልም ሳታከረው … አለ አይደል … የተማረው ላልተማረው የእውቀት አባት፣ የዕድገት ጎዳና ጠራጊ፣ የብልፅግና ፋና ወጊ

   የብልፅግና ፋና ወጊ? “ድንቄም!” አሉ ወይዘሮ ብርቄ

  ለምን አታስጨርሰኝም?

   ዘንድሮኮ አውርታችሁ ሳትጨርሱ እኛ ልናልቅ ሆነ። ትሰማኛለህ? የኢትዮዽያ ምሁር ፋናሳይሆን ህዝብነው የሚወጋው። ታላላቆቻችን የተማረ ያስተምር … ያልተማረም ይማርያሉበት ዘመን እኮ ቆየ ካለፈ። ለዛም መሰለኝ ከዕድገት በህብረትወደ ዕልቂት በህብረትባፋጣኝ የተሸጋገርነው

  ወይ ጣጣ! እና አሁን … ምሁሩ ፋና ወጊሳይሆን ህዝብ አዋጊ፤ መርሑም የተማረ ያባላ … ያልተማረም ይባላሆኗል እያልከኝ ነው?

   ደስ እንዳለህ ተርጉመው፤ የተማረ ይብላ … ያልተማረም ይበላበሚለውም ልትተካው ትችላለህ። ደሃአደግ እንደ እርድበግ ሥጋው የሚታኘክበት የጉግ ማንጉግ ዘመን ላይ ደርሰን በትርጉም ለምን እንጣላለን

  ያንተ አገላለፅ ሳይሻል አይቀርም። አንድኣንዴ እኮ

   አንድኣንዴ እኮ ምን? እጠበብብሀለሁ? lol

  ሎል … ቀላል! እንዳውም ባለፈው ጠቅላይሚንስትሩ የጥበብ ሰዎችን ሰብስበው ስመለከት ከመሐል አትጠፋም ብዬ በአይኔ ፈልጌህ ነበር

   ሰውየው ምርጫ አለብህ እንዴ?

  ኧረ የለብኝም! ምነው ሳልሰማ አጫችሁኝ እንዴ?

   ሳይሆን … “የጥበብ ሰዎችስትል፥ ምናልባት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ከሆንክ ብዬ ነው

  ተሳሳትኩ እንዴ? የጥበብ ሰዎችን መስሎኝ በቀደምለት ሰብስበዋቸው በቴሌቪዥን መስኮት የተመለከትኳቸው

   የጥበብ ሰው ማነው?

  አሁን ይኼ ጠፍቶህ ነው?

   አዎ ጠፋኝ …. ካወቅህ ንገረኝ፣ ካላወቅህ አፋልገኝ

  ጥበብ የጠራችው ነዋ የጥበብ ሰው?

   ታዲያ እኛ ሀገር ማንን ነው ጥበብ የጠራችው?

  ምንድነው የምታወራው?

   ሰራዊት ፍቅሬና አስረስ በቀለ መንገድ ላይ አይተው የጠሩት እንጂ፥ እስቲ ኣንድ ጥበብ የጠራችው … ኧረ መጥራቱ ይቅርና አንድ እንኳ በአይኗ የጠቀሰችውን አርቲስት ንገረኝ። ይህቺም ያቺም፣ ይኼም ያም፦ ሚዲያ ላይ ወጥተው እንትና መንገድ ላይ ስሔድ ተመልክቶኝ … ካፌ ውስጥ ተቀምጬ አስተውሎኝ ጠራኝና ወደ ጥበቡ አለም ተቀላቀልኩነው የሚሉን። ነው ወይስ የጥበብም ብሔር ኣማራ ነው? Art School ተፈናቅላ፣ ጎዳና ተዳዳሪ ሆና … እንዲህ መንገድ ለመንገድ እየዞረች አርቲስቶችን የምትመለምለው?

  አባቱ … አንተ ገና ብዙ ታወራለህ 

   ብዙ ማውራት አይደለም። አንተም እንደ ጠቅላይሚንስትሩ መሰሪ፣ ጭራሮውን ሁሉ ያገር ምሰሶብለህ ስታሞካሸው ገርሞኝ ነው፥ ምናልባት ድምፅ ፍለጋ ላይ ከሆንክ ብዬ ላፋልግህ

  ወንድሜ፦ እኔ ድምፅ ፍለጋ ላይ አይደለሁም። ስፈልግ ደግሞ አታስብ፥ መጀመሪያ የምታውቀውም፣ የምጠይቀውም አንተ ነው

   የሌለኝን ድምፅ ከየት አባቴ አምጥቼ ነው የምሰጥህ? ድምፅ ቢኖረን ኑሮ አለቅን!ብለን እንዲህ እሪ!ስንል አይሰሙንም ነበር ?

  አይዞህ! ለምርጫው ከየትም ፈልገው ይሰጡኃል። ለዛች ቀንማ ድምፅማበደር አይደለም፥ ልሁን ብለህ ከጠየክ ድምፃዊምያደርጉሀል። እኔ ደግሞ ከየት አባቴ አምጥቼ ነው የምሰጥህ?” ስትል አስቀደመህ የሰጠኃቸው መስሎኝ ተገርሜ ነበር

   ለማነው የምሰጠው?

  ምን አውቃለሁ፤ ስማቸው ብዙ ነው እናት” … “ሐረግ” … ምናምን

   ሐረግ ደግሞ ማናት?

  አሁን ልታደክመኝ እንጂ ሐረግጠፍታህ ነው? የሽገር ልጆች በኣድዋ ድል መታሰቢያ ዕለት፦ እዛም ሔደሽ በላሽ እዚም መጥተሽ በላሽ … ሰው ታዘበሽ እንጂ ሆድሽን አልሞላሽሲሉ የተቀኙላት? ድጋፍ ካልያዘች ብቻዋን የማትቆመው፣ የጥንት የጠዋቷ ቀሰተዳመና

   የአመሻ ኢዜማ? አሃሃ … እሱዋንማ አውቃታለሁ … የቤትስሟ ነበር የጠፋኝ

  እንዴት ይጠፋሃል? ድሮ ሳውቅህ ሳይንስ ትምህርት ላይ ጥይት ነበርክ

   ጥይት ብሆን ታዲያ … elementary school እያለን ያስተማሩንኮ ስለ ልጅነትልምሻ እንጂ የፖለቲካልምሻ እንዳለ አልነገሩንም

  በል አሁን እኔ አስተማርኩህ፤ ለውለታዬ ደግሞ ድምፅህን አጠራቅምልኝ፥ ለምርጫም ባይሆነን እንጫጫበታለን … አደባባይ  ወጥተን

   ምን ችግር አለው! ድምፄን ለአንተ ያልሰጠሁ … ቆጥቤ ምን ላደርገው ነው? “ወየው ደሜ ደሜልዘፍንበት?

  lol … የዘፈኑን ቅኔ አቶ ደመቀ ሰምተውት ይሆን?

   ከሰው አታነካካኝ፥ እኔ ወየው ያልኩት ለፈሰሰው ደሜ ነው

  ሃሃሃ ፈራህ እንዴ? አይዞህ! ብልፅግና ከምርጫው ቦኃላ ፈራሽ ናት

   ፈሪ ፍርፋሪ ለቃቃሚው ብአዴን ብቻ ነው። ወንዱ የኣማራ ሚልሽያ ግድሎ ያለፈውን አስክሬን እንደልማዱ ለቃቅሞ እየቀበረ: “ህወሃትን ገድለን ቀብረነዋል!” እያለ የሚፎክር … የድል ድንኳንሰባሪ

  I know … አንተማ አትፈራም! ግን ለማንኛውም የአዳጋ ጊዜ ተጠሪህን በደማቁ አጽፈህ ተንቀሳቀስ

   አደጋ አድራሹ መንግስት በሆነበት ሀገር ማን ተርፎ ነው ለማን የኣደጋ ጊዜ ተጠሪየሚሆነው? ባይሆን አዲሱ መታወቂያ አደጋ አድራሽ …. ” የሚል ፅህፈት ካልው መንግስትን በድርቡ አስመዘግበዋለሁ

  ከሰሜን እስከ ደቡብ … ብሔር ብሔረሰቦች ኣንድ ሆንን በለኛ። በል … መልካም ሰንብት!

   አሜን አብረን መልካም እንሰንብት!

Comments are closed.