Post

የኮሎኔሉ ‘ግልፅ ጦርነት!’

By Admin

የሰው ልጣጭ ነው ያሉት አንድ እናት። ህፃኑ ተቀብሮ የእንግዴ ልጁ (ልጣጩ) ሲያድግ፤ የራስቅል እንዲህ በአንጓል ሳይሆን በአንጀት ይሞላና፥ ሰው ለህሊናው ሳይሆን ለሆዱ ማደር ይጀምራል።

ትዝብቴን በአጭሩ ላስቀምጥ፦

ደቂቃ 0:03:40 – 0:03:55

ሲጀመር፦ ባልደራሱ በSaint Mary College የምርቃት በዓል ጩኽት ተረብሾ ስብሰባውን ማስተላለፍ፥ አልረበሽም ብሎ ካሰበም በተያዘለት ቀንና ሰዓት ዝግጅቱን መቀጠል በእርሱ (በባልደራሱ) ምቾትና ምርጫ ብቻ የሚወሰን ሆኖ ሳለ፥ አንረበሽም እንቀጥላለንብለው ሲወስኑ፥ የሆቴሉ መስተዳድር የፀጥታ ሀይል መጥራቱ የሴራውን ጫፍ እንደሚያስይዘን አይገባቸው ይሆን? ለነገሩ አንጀት ማላመጥ እንጂ እንደ አእምሮ ማሰብ የት ይሆንለታልና ይህን ያገናዝቡ?

ደቂቃ 0:07:00 – 0:07:40

ሲቀጥልም፦ ግለሰቡ Saint Mary ኮሌጅ የምረቃ ዝግጅቱን አስቀድሞ እንደያዘ ተናገሩ፥ ለወትሮውም የምረቃ ዝግጅት ሲኖር …”እንደዚህ ሁኔታ ባለበት ጊዜ ሁልግዜ አንደኛውን አንይዝም ብዙ ግራጁዌሽኖችንአድርገናል እኛ  ብለውም ተናዘዙ። ልብ አድርጉ … ‘ከዚህ በፊት ሁለቱንም ኣዳራሽ አናሲዝም እንዲህ አይነት ትልቅ የድምፅ መሳሪያም አይተን አናውቅም ብለው ሲገዘቱ፤ ሁልጊዜ፦ ሁለቱንም አዳራሽ ላለማስያዝ ምክንያታቸው የድምፅ መሳሪያው መተለቅና ማነስ ሳይሆን፥ ፕሮግራሙ ’graduation’ መሆኑ ብቻ እንደሆነ በራሳቸው አንደበት እራሳቸው ላይ እየመሰከሩ ነው። ከሰውየው የደቂቃ ስብዕና ትንተና ተነስተን ልናምናቸው ብንቸገርም … ‘ይሁንብለን እናዳምጣቸውና … .

ታዲያ የSaint Mary ኮሌጅ ዝግጅት የምረቃ በዓልመሆኑ እየታወቀና፥ የትምህርት ተቋሙ ኣንደኛውን አዳራሽ ከባልደርሱ በፊት በፊት በፊት ቀድሞ እንዳስያዘ እየመሰከሩ፥ የምረቃ በዓሉ ሊከናወን ኣንድ ቀን ሲቀረው ሁለተኛውን አዳራሽ ለባልደራሱ ለማከራየት ለምን ወሰኑ? ይህም ሌላው የሴራውን ጅማት ጫፍ የሚያስጨብጠን … ከቀጫጫ አእምሮ የሚወጣ ወፍራም ውሽት ነው።

ጎበዝ እኔ ግን የከተማው ከንቲባና ጠቅላይ ሚንስትሩ፥ ባልደራሱ የሚመሽግበትን የስብሰባ አዳራሽ ለማወቅ እስከ ምሽቱ ሦስት ሰዓት ድረስ ሲዳክሩ ማምሽታቸው አስገርሞኛል። በዚህና በተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ሰፋ አድርጌ እስክመለስ፥ ለኣዲስ አበቤው ኣንድ ጥያቄ አለኝ፦ እስከ መቼ ድረስ ነው ለኮሎኔሉ ግልፅ ጦርነት ውስጥ እንገባለን ዛቻ አዲስ የምትሆነው? ይልቅ ከሰሞኑ እመለሳለሁ።

*video source: Fana Television

Comments are closed.