
By Admin
ዱሮ ዱሮ እብድ ድንጋይ ከመሬት ላይ እየለቀመ ሲወረውር ነበር የምናውቀው፥ ዘንድሮ ግን በህወሃት Growth and Transformation Project (GTP) መርሕ፦ ከጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት ፈንጂ በፊርማ እያወጣ ህዝብ የሚፈጅ ልማታዊ እብድ ተፈጠረ ማለት ነው? እንደው ለነገሩ እንጂ … ጠቅላይ ሚንስትሩ፦ ጉልበትና አቅማቸውን ብቻ ሳይሆን አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ ህይወታቸውንም ጭምር ለዚህ ህዝብና ሀገር መስዋዕት ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ፣ ፍርሃትና ሞት የማያስደነግጧቸው ወታደሪዊ መኮንን መሆናቸውን ለማን ይነግሩዋል? ቦምብ እና Kalashnikov (ክላሺንኮቭ) ታጥቀው አይደለም፥ የሙሴንም በትር ነጥቀው ቢመጡ ይህን ለውጥ ማቆም አይቻልም! ይሰማል?!