Post

ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

ጥቁሩ ዘለንስኪ (The Black Zelenskyj)

By Admin

ከጥቂት ቀናት በፊት … William Scott Ritter ያዘጋጀውን ‘Agent Zelenski’ የሚል የኣንድ ሰዓት ከሃያ-ሁለት ደቂቃ እርዝማኔ ያለውን documentary ፊልም ተመልክቼ እንደጨረስኩ … ‘ጥቁሩ ዘለንስኪ’ ፊቴ ላይ ድቅን አለ። በእርግጥ … አሁን ሀገራችን ላይ ባለው ነባራዊ ሁኔታ፥ ለምዕራባውያኑ ፍላጎት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ በማገልገል የወኪል ዘለንስኪን መሳይ ተግባር እየከወነ ያለው ግለሰብ ጠቅላይ ሚንስትሩ ይሁኑ ወይንስ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ለመወሰን ትንሽ ሰከንዶችን ማጥፋቴ አልቀረም። በመጨረሻ ግን … በጥቂት ግራም ልዩነት  ምርጫዬ ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢያዘነብልም፥ በዚህ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት በመነገድ ረገድ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚጫወቱት ሚናም ቀላል እንደማይሆን በደንብ እገነዘባለሁ።

ይህን ዶክመንተሪ ፊልም ሙሉ በሙሉ መመልከት … የዩክሬሩ Volodymyr Zelenskyj እንዴት ወደ ፕሬዚደንትነት ስልጣን እንደመጡ፣ የትና በማን  በወኪልነት ተመልምለው እንደተሰማሩ ጠለቅ ያለ ምልከታ ለመስጠት ቢረዳም፥ ወሳኝና ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ተነፃፃሪነት አላቸው ብዬ ያሰብኳቸውን … የምዕራቡ ዓለም ለፕሬዘደንቱ በኣስቸኳይ እንዲተገበሩ የሰጣቸውን ኣሥር ተግባራት (Tasks) ብቻ በመንቅስ ቪዲዮውን እንደሚከተለው አሳጥሬ አቅርቤዋለሁ።

ተመልካች የራሱን ግንዛቤ እንዲይዝ ይረዳል ብዬ በማሰብም … ከእያንዳንዱ ተግባር (task) በተጓዳኝ በሀገራችን ውስጥ የተፈፀሙና እየተፈፀሙ ናቸው ብዬ የማስባቸውን ግልፅ እውነታዎች በኣጭር ዝርዝር አስቀምጫቸዋለሁ።


TASKS given to Volodymyr Zelenskyj:

 1. THE RUSSIAN LANGUAGE. To eliminate the Russian language. (ተነፃፃሪ ተግባር: የአማርኛ ቋንቋን ማዳከምና ማጥፋት)
 • በኣዲስ አበባና በክልል ትምህርት ቤቶች ውስጥ የአማርኛ ቋንቋን የማዳከም እንቅስቃሴ። በትግራይና በኦሮምያ ክልል ውስጥ በሚገኙ በማናቸውም ደረጃ ባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኣማርኛ ቋንቋ ትምህርት እንዳይሰጥ ማገድ። በኣማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጭምር የኣማርኛ ቋንቋ ጥናት ተቋማትን መዝጋት። በዶክመንተሪ ፊልሙ ውስጥ በቀረቡ ምሁራን አስተያየት መሰረት ይህ ቋንቋን የማዳከም ተግባር ለ ‘ethnic cleansing’  ወሳኝና የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው።
 1. SPLIT IN UKRANIAN ORTHODOX CHURCH. To finalize the Church split. (ተነፃፃሪ ተግባር: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ክፍፍል)
 • አሁን እንደሚታየው በመንግስት ድጋፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቢቻል በእያንዳንዱ አልያም በኦሮሚያና በትግራይ ክልል ደረጃ ከፋፍሎ ማደራጀት። በዶክመንተሪ ፊልሙ ውስጥ በተጠቀሰው አስተያየት መሠረትም … የዚህ ተግባር ዋነኛ ዓላማ ከቤተክርስቲያኒቱ መጠሪያ ላይ ያለውን ‘Russia’ (ወይንም ‘ሞስኮ’) የሚለውን ስም መፋቅ እንደሆነ ሁሉ … ወደ ሀገራችን ነባራዊ እውነት ስንቀይረው ደግሞ … ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ መጠሪያ ስም ላይ ‘ኢትዮጵያ’ የሚለውን ገላጭ መደምሰስ ይሆናል።
 1. REWRITING HISTORY. (ተነፃፃሪ ተግባር: ታሪካዊ እሴቶችን ማፍረስና ታሪክን ቢቻል እንደ ኣዲስ አልያም አዛብቶ መፃፍ)
 • ይህ ካለፈው የህወሃት አገዛዝ ጀመሮ እየተሞከረ ያለ ክንዋኔ ቢሆንም፥ በኦህዴድ መንግሥት ግን በስፋትና በኣፋጣኝ መሬት ላይ እየወረደ ያለ ተግባር ነው። ለምሳሌም፦ የኣድዋንና የምኒልክን ታሪክ ማዛባት፣ የበዓሉን አከባበር ልማድና ቦታን መቀየር፣ ነባር ታሪካዊ ቅርሶችን (ሓውልቶችን፣ ቤተ-መንግስቶችን፣ ቤተ-እምነቶችን) ማንሳትና ማፍረስ፣ ሰንደቅ-ዓላማን መቀየርና ቀድሞ ከሚሰቀልበት ቦታ (ከመኪናና ከልብስ ጥለት ላይ ጭምር) ማስወገድ፣ ታሪክን የሚያውቁና የሚያስተምሩ ምሁራንን (አቶ ታድዮስ ታንቱን ጨምሮ) ማንገላታትና ማሰር … ወዘተ የመሳሰሉት ተግባራት እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ናቸው።
 1. UKRANIANS BANS DOMESTIC TV CHANNELS. (ተነፃፃሪ ተግባር: የግል ጋዜጣና ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና)
 • ምንም እንኳ በሀገርችን ውስጥ በግለሰብ ደረጃ አየር ላይ የሚውሉ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ባይኖሩም፥ የመንግስትን የውጭ ተልኮ አስፈፃሚነት የሚያጋልጡና የሚቃወሙ ጋዜጦችን መዝጋትና ጋዜጠኞችንም ማሰር የእለት ተእለት ተግባር ነው። የፍትህና ሌሎች ጋዜጦች ህትመት መቋረጥ፣ በስፋት እየቀጠለ ያለው የጋዜጠኞች እስርና መሰደድን እንደ አስረጅ መውሰድ ይቻላል።
 1. BAN THE OPPOSITION. (ተነፃፃሪ ተግባር: ተቃዋሚ ድርጅቶችና ግለሰቦች ማስወገድ)
 • ይህን በተመለከተ… ከኣማራ እስከ ጉራጌ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎችና አመራሮች ላይ በሰፊው እየተፈፀመ ያለው የግድያ፣ የማፈን፣ የድብደባና እሥር ተግባር ግልፅ ማስረጃ ነው።
 1. MILITARY BIOLABS.
 1. MERCENERIES. (ቅጥ ያጣውና ቅልጥ ያለው የህወሃትና የኦህዴድ ቅጥረኛነት)
 • መጥፎ እድል ሆኖ ካለፈው የህወሃት አገዛዝ ጀምሮ እስከ አሁኑ የኦህዴድ መንግስት … ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም የፖለቲካ ፍላጎት አስፈፃሚነት መዳፍ ሥር ለመውጣት አልተቻላትም። ኢትዮጵያ የኣሜሪካንን ጦርነት ስትወጋ ቀላል በማይባል ቁጥር የዜጎቿን ህይወት አጥፍታለች – አስጠፍታለች። አሁንም ያለው እውነት ከዚህ የተለየ አይደለም። ለዚህ ማስረጃው ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትሩ በኣፋቸው ‘ለኣሜሪካን ጥቅምና ደህንነት መስዋዕት እሆነለሁ’ ሲሉ መነበባቸው ነው።

ከዚህ ባሻገር … በኣፍሪካ ቀንድ ያሉ ሀገራት በቸልታ ሊመለከቱት የማይገባው ስጋት፣ የወልቃይትና የኣካባቢው ይዞታ ነው። ይህ መሬት በኣንድም ይሁን በሌላ ምክንያት በቅጥረኛው ህወሃት አገዛዝ ሥር የሚወድቅ ከሆነ … ለይመሰል በሚፈረም ወታደራዊ ስምምነት … ሰዓታት እንኳን ባልሞላ የጊዜ ፍጥነት …  የኣሜሪካን ወይንም የምዕራባውያን ጦር በቦታው ላይ ሊሰፍር እንደሚችል መጠርጠር ተገቢ ነው። የውጭ ወራሪዎች ከ’ምዕራብ ትግራይ’ ይውጡ የሚል የኣዛኝ ቅቤ ኣንጓች ግፊት ዓላማው ወታደራዊ-ሰፈራ ነው። ይህ ደግሞ ከመንግሥት ለውጥ (በእነርሱ አጠራር ከ Regime change) እስከ ሀብት ስርቆት (resource looting) ድረስ በቀጠናው ላይ የሚፈፅሙትን ዓለማቀፋዊ ወንጀል ቀላል ብቻ ሳይሆን ስውርም እንዲሆን ይረዳል።

 1. A LEGALIZATION OF NAZISM.
 • በኣንድ ዘርና ሀይማኖት ላይ ያተኮረ የጥላቻ ንግግር፣ የጅምላ እስር፣ ግድያና መፈናቅል እንደ በጎ ተግባር ተቆጥሮ ከክልል መሪዎች እስከ ተራ የመንገድ ላይ ቦዘኔዎች በኣደባባይ በከፍተኛ ድምፅ የሚደሰኩርበትን መድረክ ማየት እንደ Latinos carnival  አዝናኝ ትዕይንት እየሆነ መጥቷል። የሰማናቸውና የምንሰማቸው “የጀርባቸውን አጥንት ሰበርነው፣ ዓይናቸውን አስለቀስነው፣ ህጋዊ ድሆች አደረግናቸው” ወዘተ የሚሉ … ህዝብን ለኣረመኔያዊ ተግባር ማነቃቂያ የሚውሉ ቃላቶች … ከቀድሞው የኣውሮፓ ፋሽስትና ናዚዝም ስርዓት መፈክር የሚለዩት በትርጉማቸው ሳይሆን በተነገሩበት ቋንቋና ዘይቤ ብቻ ነው።
 1. SALE OF LAND. (ተነፃፃሪ ተግባር: የጫካ ከተማ፣ ሸገር city complex እና ሌሎች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች)
 • ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የኦህዴድ አገዛዝ በከፍተኛ ደረጃ ደሃውን በማፈናቀል ተጠምዶበት ያለው ንግድ መሬት ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ  ‘እናንተ ገንዘብ አልሰጣችሁኝም ስለዚህም ምንጩንና ባለቤቱን ልትጠይቁኝ አትችሉም’ የሚሉን … ነገር-ግን ቀላል  የማይባል የመሬት ሽፋን እየወሰዱ ያሉት ፕሮጀክቶች ይህን እውነት አስረጂዎች ናቸው። በቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነቡት የጫካ ቤተ-መንግስት፣ የሸገር ከተማ ኮምፕሌክስና ሌሎች ፕሮጀክቶች ባለቤትነታቸው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ (በሀገር በቀል ድርጅቶችና ኢትዮጵያዊ ዜጎች ስም)  ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች እንደሆነ አያጠራጥረም።
 1. SIGN AN AGREEMENT THAT UKRAINE RECEIVES WEAPONS AND EQUIPMENTS ON CREDIT.
 • እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑት የሥርዓቱ ባለሟሎች ውጪ አጠቃላይ ዜጋው ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የውጭ ዕዳ ክብደቱና የገንዘብ ግሽበቱ ቀጥተኛ ተጠቂ ነውና ይህን በተመለከት ምንም ማለት የሚኖርብኝ መስሎ አይሰማኝም። ይሁንና ግን … አሁንም ቢሆን መንግሥት በሥልጣኑ ለመቆየት IMF እና World Bank’ ን ለመሰሉ አበዳሪ ተቋማት አስገዳጅ inhumane pre-conditions እጅ በመስጠት የሚቀበለው ብድር … ቢያንስ መጪው ሁለት ወይንም ሦስት ትውልድ ለምዕራባውያኑ በዕዳ የተያዘ ‘ተንቀሳቃሽ ንብረት’ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርገዋል።

ሙሉ ዶክመንተሪ ፊልሙን ለመመልከት ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ መጠቀም ይቻላል።

A Scott Ritter Investigation: Agent Zelensky

“William Scott Ritter Jr. (born July 15, 1961) is an American author, pundit, former United States Marine Corps intelligence officer and former United Nations Special Commission (UNSCOM) weapons inspector.

Ritter served as a junior military analyst during Operation Desert Storm. He then served as a member of the UNSCOM overseeing the disarmament of weapons of mass destruction (WMD) in Iraq from 1991 to 1998, from which he resigned in protest. He later became a critic of the Iraq War and United States foreign policy in the Middle East.”

Comments are closed.