Post

ፋኖ – የኣባቱ ልጅ!

ፋኖ – የኣባቱ ልጅ!

By Admin

Chuncheon – ከደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ Seoul በኣንድ ሰዓት የየብስ ትራንስፖርት ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ። ከተለያየ ሀገራት የተሰባሰብን ግለሰቦች ትምህርታዊ ጉዟችን መዳረሻ ካደረጋቸው ሀገራት መካከል South-Korea ኣንዷ ነበረችና አጋጣሚውን በመጠቀም የሀገሪቱን ብሔራዊ ሙዚየም በመጎብኘት ላይ ነን። በግሩፕ የተሰጠንን አስጎብኚ ( guide ) በመተው እኔና ሁለት ጎደኞቼ ወደ-ኋላ ቀረት በማለት … በየቅርሥና ቅርጹ ራስጌና ግርጌ የተለጠፈውን መግለጫ በማንበብ የየራሳችንን ግንዛቤ በመለዋወጥ ላይ ሳለን …  ከኣስጎብኚያችን ጋር ከፊት የቀደሙት ሌሎች ጎደኞቼና አስተማሪዎቼ ድንገት ወደ-ሗላ በመዞር በኣንድነት ስሜን ጠሩት።  

ፊታቸው ላይ የማየውን ፈገግታ ምንጭ ለማውቅ እኔና ከእኔ ጋር የነበሩት ሁለት ጎደኞቼ ፈጠን ፈጠን ብለን በመራመድ ስንቀላቀላቸው ግን … በዜግነት ደቡብ ኮሪያዊ የሆነው አስጐብኚ  እጁን ለሰላምታ እየዘረጋልኝ ‘are you from Ethiopia?’ ሲል በመገረም ጠየቀኝ። ነገሩ ትንሽ ግር ቢለኝም ‘አዎን … ኢትዮጵያዊ ነኝ’ ስል መለስኩለት። ከዛም … ከላይ እንደ feature image የተጠቀምኩትን ቅርጻቅርጽ እየጠቆመኝ … የ’ጥቋቁር’ ሰዎቹን ማንነትና በ’ነጮቹ’ ሀገር በድል አድራጊነት ኩራት በክብር የቆመውን ወታደር ጀብድ ገለፃ በሚያደርግበት ወቅት … ከግሩፑ መካከል ኣንድ ኢትዮጵያዊ መኖሬ እንደተነገረውና ጎደኞቼም ይህን ታሪክ “ሊያበስሩኝ” ተሽቀዳድመው እንደጠሩኝ ተረዳሁ።

አስጓብኚው እኔ ከማውቀው በላይ ኮሪያ ሰለዘመተው ስለ ቃኘው Battalion ዘርዘር ባለመልኩ ገለፃውን ሲያቀርብ …  ነፃ አውጪው ዘማች እኔው እራሴ የሆንኩ መስሎ እስኪሰማኝ ድረስ … የጎደኞቼና የአስተማሪዎቼ አይኖች ሙሉ በሙሉ ሊባል መሚችል መልኩ እኔ ላይ እንደ ተተከሉ ነበር። ለነገሩ በኣያት ቅደመ-ኣያቶቹ ታሪክ የማይኮራ ኣንድም ባንዳ አልያም እንደ ጥርስ መፋቂያ እንጨት ግንዱ እየተቆረጠ የተራባ  – ዘር አልባ! ነው።

ከሁለት ዓመት በላይ በፈጀው የኮሪያ ጦርነት  ከ 3000 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች በጦርነቱ ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፥ ከእነዚህ መካከል ደግሞ ያኔ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ምድር እስክትጠቀለል ድረስ ለመላው ኢትዮጵያዊ  ክብርና ሞገስ የሚሆኑ 536 ዘማቾች ቆስለው 212ቱ ደግሞ ተሰውተዋል – ነፍስ ይማር! ከሁሉ በላይ የሚያስገርመውና ለዛሬ ኣጭር ፅሑፌም መንደርደሪያ ሃሳብ ላደርገው የወደድኩት እውነት ደግሞ … ኣንድም ኢትዮጵያዊ እጁን ለጠላት ጦር አለመስጠቱና በምርኮኝነት አለመያዙ ነው። ከእኔ ገላፃና ትርጉም በተሻለ የደቡብ ኮሪያ የጦር መታሰቢያ ኢንስቲትዮት እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ይሰጣል፦  

A total of 122 Ethiopian soldiers were killed, and 536 were wounded. There were no prisoners of war.

Overall, as a unit, the Ethiopians never lost in combat during the war and earned the US Presidential Unit Citation. The Ethiopian soldiers also deducted a portion of their monthly salary to support Korean children orphaned by the war. (Source: Korean War Memorials)

ደም ፦ ከዘር ወደ ዘር የሚዛወር፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገር ፈሳሽ አሻራ ነው። ለዚህም ነው፦ ግማሽ መንፈቅ ሊሞላው ጥቂት ወራት በቀረው የኣማራ ክልል ጦርነት የኦህዴድ ዘረኛ ሠራዊት ኣንድ ፋኖ መማረክ … ከሰማየ-ሰማያት ኮከብ እንደማውረድ ሆኖ የከበደው። ፋኖ ከነፍሱ ይልቅ ለእጁ አብልጦ ይሳሳል። በትግራዩ ጦርነት፦ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ ከተራ ወታደር እስከ ኮሎኔል፣ ባለሥልጣን ሳይቀር በሰልፍ ደርድሮ  “ተመልከትሉኝ! በብር የምለውጠው ምርኮ” እያለ እንዳልፎከረ፥ ለኦህዴድ ሠራዊት ዛሬ ፋኖ ‘መንፈስ’ ሆኖበታል … የማይያዝ! የማይጨበጥ!

እናቱ እህ! ብላ አምጣ የወለደችው እና የሰፈር አዋላጅ ማንቁርቱን አንቃ ጎትታ ያወጣችው ወንድ የሚለየው እንዲህ ሜዳው ላይ ሲገናኙ ነው። ፋኖ ፦ በምድር የሰማያዊቷ ከንዓን አምባሳደር ሆኖ የተሾመው ጳጳስ ቤተመቅደሱን ንቆ ቤተመንግስት በሚቀድስበት አሳፋሪ ዘመን … የምስኪኑን ደም፣ የደሃውን እንባ ለመታደግ የተነሳ የኣምላክ ሰይፍ ነው። እናም … “ለእግዜሩም እግዜር ይሰጠው!” ብለን በዚች አጭር ግጥም ብንለያይስ?

እንኳን የሚጨበጥ … የሚያዝ በምርኮ
ጠምዝዘው  የሚያስሩት … በቃጫ፣  ሲባጐ

በዲናር ደልለው  … ቢመኙ ሊስሙት
እንደ አቡኑ መስቀል … ከፍለው ሊሳለሙት
ፋኖ የኣባቱ ልጅ
መች አለውና እጅ?

ይሄ የኣማራ ኩራት … ቃታ ቀለበቱ
አጥልቆባት እሳት … ትፋጃለች ጣቱ!

N.B. ጥራትን ታሳቢ በማድረግ በገላጭ ምስልነት የቀረበው ፎቶ ከግለስብ ካሜራ ሳይሆን ከኮሪያ ጦርነት መታሰቢያ ድህረ-ገፅ ላይ የተወሰደ ነው።

Comments are closed.