Post

Adios Addis, Kudos Los Cabos!

Adios Addis, Kudos Los Cabos!

By Admin

ለኣማርኛ ፅሁፍ የእንግሊዝኛ ርዕስ በመጠቀሜ ይቅርታ መጠየቅ ግድ ይለኛል።

አንድ ጤነኛ ሰው ተውልዶ ላደገበት ሀገር ቀርቶ በዓይኑ ላላየውም ምድር ብጥብጥ ይመኛል ብሎ ማሰብ ቢከብድም፥ በብሔርተኝነት ተርብ ዜጎችን መንደፍና ማስነደፍ ግን ከሁከትም አልፎ ደም መፋሰስ፣ ከመመታታትም ተርፎ ሞት እንደሚያስከትል መናገር ግን ህመም አይሆንም።

መስከረም ሁለት ቀን ተጠርቶ የነበረው የኣዲስ-አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሰልፍ በመንግስት ሀይሎችና በከተማዋ አስተዳደር መታፈኑ ብቻ ሳይሆን፤ ተረኞች ነን የሚሉ የተደራጁ ህግ አስከባሪ አካላትም ጭምር መንገድ በመዝጋት የወሰዱት ግልፅ ጎጣዊ ጥቃት ይዞት የሚመጣው መዘዝ ሲታሰብኝ … ደህና ሰንብች አዲስ አበባ – ጤና ይስጥልኝ ሎስ ካቦስ! አስባለኝ። Los Cabos የምድራችን ተቀዳሚ የወንጀል መዲና በመሆን የምትታወቅ የሜክሲኮ ከተማ ስትሆን፥ ለዚህ መጥፎ ዝናዋ አስተዋፆ ያደረጉት የከተማዋ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግብአቶች (inputs) ደግሞ ዛሬ አዲስ-አበባ ላይ እጅና እግር እያወጣ ከመጣው እውነታ ጋር በእጅጉ ይመሳሰላሉ።   

ዝርዝር መነፃፅሩን እያንዳንዱ አንባቢ በግሉ ከጥልቁ የgoogle ባህር ውስጥ ባሻው መጠን እንዲጨልፍ ብተወውም፥ በኣዲስ አበባ ከተማ በግልፅ የሚታየው ከፍተኛ የህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና ክምችት፣ ብሔርተኛ መሪዎች ህብረ-ብሔራዊውን ነዋሪ ለመጠቅለል ያላቸው ጉጉት ብቻ ሳይሆን የአደባባይ ዛቻ፣ በስልጣንና ጥቅም ክፍፍሉ ላይ በድፍረት ያለሀፍረት የነገሰውን ተረኝነት፣ ይህ መቡዋደንና መከፋፈል መቐሌ ለሸመቀው አጥፍቶ ጠፊ አንጥፎ የሚጠብቀው ምቹ ቀይ ምንጣፍና ወዘተን ለተመለከተ ግለሰብ፥ Addis … ከዚህ ቦኃላ በምትሸከመው ጥቂት መንግስታዊ የጥፋት policy ወደ Los Cabos እንደምትጓዝ ለመተንበይ ነብይ ሆኖ መቀባት አይጠበቅበትም።

ታስቦ የነበረው የ”ባልደራስ” ሰላማዊ ሰልፍ በኣዲስአበባ መንግስት ግልፅ አድሎ፣ በኦሮሚያ ክልል ቄሮና የፖሊስ ተጋድሎተስተጓጉሎ ቀረ የሚለውን ዜና ስሰማ፥ በእውነት አቶ ታዬ ደንደአ ይለይልን ያሉትን አባባል ከወደድኩት በላይ እጥፉን ወደድኩት። አዎ ይለይልን! እስከመቼ እያነከስን? ያኔ … ሲለይልን… እዛም ቤት እሳት አለከሚለው አባባል በተጨማሪ መማማሪያ የሚሆኑን፦ እዛም ሰፈር ወጣት አለ” …  “እዛም መንደር ሺህ የሚመልስ ሽመል አለ! ሌላም ብዙ ብሒሎች ይኖሩናል።  

ሀያሉን በሀይል ምስኪኑን በፍቅር መመለስ ስብዓዊ ብቻ ሳይሆን አምላካዊም ባህሪ ነው። ጨፈቃን በጨበጡ ጭፍኖች የሚጨፈጨፈው አቶ ታዬ ደንደአ እንዳሉት ዱላ መጨበጥ የማይችል ቆማጣ ” … በእኔ ትርጉምም አዴፓ ብቻ ነው። በነገራችን ላይ አቶ ታዬ ደንደአ ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት … ይላል ኣማራ በማለት ያቀበሉንን ተረት መሰል ተረብ በሚገባ ልብ ብለናል። ቃላቶች የተፃፉበትን ቅርፅና ቀለም ተመልክቶ የሚያነብ ዓይን ብቻ ሳይሆን፥ ውስጣዊ ጠረናቸውንም በሚገባ አሽትቶ መልካምና መጥፎ ማዕዛቸውን የሚለይ አፍንጫም ጭምር ያለን ብዙዎች ነን። አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ይኽን መሣይ ቅኔን ለመፍታት ብቻ ሳይሆን ለመቋጠርም አቅም አያጥረንም።

ዛሬ፦ አዲስ አበቤውም ሆነ የትኛውም ሰላም ወዳድ ዜጋ ሊረዳው የሚገባው ሐቅ ይህ ነው፦ ዱላን እንቅደ ጨላ ጨብጦ ነፍስ ሊያጠፋ መጋላ የወጣ በአቦም ሆነ በአባገዳ ምልጃ ሊመለስ አይችልም። እምነትም ሆነ ግብረገብ የሌለው ሰብ፥ በአማልክት ክብር፣ በሽማግሌዎች ምክር የሚለዝብ ልቦና አይኖረውም። እምነት ያለው፦ የእምነት ተቋማትን እንደ ሰንደል አክስሎ አያጨስም፤ ግብረገብ ያለው፦ የሰው አካልስጋ እንደታጠበ ሽማ ዘቅዝቆ አይሰቅልም፣ ደግሞም ሻሸመኔ ላይ እንዳየነው፦ እድሜ ያጎበጠው የአዛውንቶችን ጀርባ እንደ እንስሳ በእርግጫ አይነድልም።

እንደ እኔ የግል እምነት፦ ለሰው ዘር ነፃነትን ከነፈገች ሀገር ይልቅ መብትን የምታከብር መንደር እጅግ ትሰፋለች። በሰፊዋ ሀገር ተከባብረን መኖር ካልቻልን፥ በጠበበ ሰፈር ሲብስም አጥር ተደፋፍጦ መኖር ግዴታ ይሆናል እንጂ ማንም የማንንም አከርካሪ ሰብሮ ቀርቶ ተደግፎ አይቆምም።

ኣማራም ይሁን ጋሞ፣ ትግሬም ይሁን ኦሮሞ ሰብዓዊ መብትን በተመለከት በሚደረገው ማንኛውም ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ ድልድል ውስጥ በወርድና በቁመቱ ተለክቶ ልዩ ጥቅም ሊያገኝ ይገባል የሚል አመለካከት ንፁህ ብሔርተኝነት ነው። በኣንድ ሀገር ዜግነት ውስጥ ታቅፈን ኢትዮጵያዊየሚል የጋራ መገለጫ እስካለን ድረስ፥ ኣርባ ሚልየንም እንሁን ኣርባ ብቻ፥ የብሔር ቁጥር በኢትዮጵያዊነት ለሚገኝ መብትና ጥቅም መመዘኛ ሊትር እና ሜትር ሆኖ ሊቀርብ አይገባም።

ይህ መንግስት ትላንት በእንቁላል ደረጃ ተውልዶ ዛሬ በስፋት የተፈለፈለውን የብሔርተኝነት እጭ በቶሎ መቅጨት ካልቻለ፥ ነገ የእድገት ደረጃውን ጨርሶ ክንፍ አውጥቶ መብረር ሲጀምር፥ አዲስ ብቻ ሳትሆን ናዝሬትም የKwaZulu-Natal, Durban ከመሆን አትድንም። የአቶ በቀለ ገርባ የኣዳማ OPDO ሙሉ በሙሉ ኣማራ ነው ትረካ ገደምዳሜ ትርጉም ያልገባው አዳሜ … የደቡብ አፍሪካዋን ከተማ ወቅታዊ ወግ ልብ ይበል!

Comments are closed.