
ENGLISH POSTS

አማርኛ መጣጥፎች

LIKE US ON FACEBOOK
SEARCH US HERE

ተረቱ እንኳን፦ “ሊበሉ ያሰቧትን ኣሞራ … ” ነበር። ዘንድሮ ግን፦ ሊበሉ ያሰቡትን ኣማራ “ነፍጠኛ” ነው እያሉ እንደ እንስሳ በካራ ይበልቱት ጀምረዋል። ግን ጎበዝ … ቤንሻንጉል ከኢትዮጵያ ድንበር ምን ያህል ይርቃል? ከመሬት ጋር አብሮ ዞሮ መተከል የግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ሆነ እንዴ? እንዴት ነው የኢትዮዽያ መንግስት እዚህ ክልል ውስጥ ገብቶ ህግ ማስከበር የተሳነው? ትላንትናስ እሺ … …
የህወሃት ትግል ከጥንስሱም ቢሆን ትርጉም አልባ እርጉም ነበር። ጭካኔ እንጂ ጫካ ያገባቸው፥ በደልና ግፍ አልነበረም ወደ በረሃ የገፋቸው። አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ እንዳለው፤ “ወንበዴ” ነበሩና ወደ ውንብድና ተመልሰው ይኸው ዛሬ ሞት እና ሞርታር በየበረሃው እየማረካቸው ነው። ትላንት … የአዛውንቱ የአቶ ስብሃት ነጋ እጅ፥ ማጌጫ ሳይሆን መቀጫ ቀለበት አጥልቆ ስመለከት … በሀይልና ሀብቱ ሲኩራራ ሰባት …
ሄሎ ጤና ይስጥልኝ፤ ምነው ደጅ አስጠናኸኝ? ኣማሮች የውጭ ስልክ ለማንሳትም ከብልፅግና ፓርቲ ፈቃድ ትጠይቃላችሁ እንዴ? እኔ እንኳን የሰማሁት ወደ ስልጣን ለመምጣት ብቻ ነበር Sorry, ሥራ ይዤ ነበር … ላዛ ነው ቶሎ ያላነሳሁት ምን ዓይነት ሥራ ነው ስልክ የማያስነሳ? ተሰብስባችሁ ሰንደቅ–ዓላማ እየሰቀላችሁ ነበር እንዴ? ሰውየው፥ ዘንድሮ ህዝብ ተሰብስቦ የሚሰቀለው ሰንደቅ–ዓላማ ሳይሆን …
ፅሑፌን፦ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ነፍስ ይማር ብዬ መጀመር አግባብ ነው። ለቤተሰቡና ወላጆቹ፣ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እመኛለሁ። ወንድ ልጅ ላመነበት እውነት ቢገልም ቢገደልም ጀግና ነው! አሳፈሪውና የፈሪ ምግባር ግን ማስገደል ነው። ትንሽ ከራርመን፦ በመዲናችን አዲስ አበባ የወዳጅ አዝማድ፥ በአጠቃላይ የነዋሪዎቿ ህልፈተ–ህይወት በድንገት ሲሰማ፥ ለከተሜው ተለምዷዋዊ ጥያቄ የሚሆነው “ታሞ ነበር ? ” ሳይሆን “ማን ገደለው …
“ከተኮሱብን እንተኩሳለን!” … ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ይላል መፅሐፉ፤ እኔ ደግሞ በግሌ፦ የፖለቲካ ሁሉ መቅደም ማህበረሰብን ማክበር ነው እላለሁ። ለዜጋ ብሎም ለህብረተሰብ ክብር የሌለው የዜግነት ፓለቲከኛ፥ ቧልተኛ እንጂ ሌላ ምን ይባላል? ጊዜው፦ ህወኃት በአፍጢሟ ልትደፋ እየተንገዳገደች የነበረችበት ወቅት ነበር … 2016። የአርበኞች ግንቦት–ሰባት ሊቀመንበር፦ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ለህዝባዊ ስብሰባ ጀርመን …